

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ"
በአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን የተቋቋመው የኢንስፔክሽን ቡድን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመገኘት በ4 ወር የተሰሩ ስራዎችን መልከታ ማድረግ ጀምሯል።
የኢንስፔክሽን ቡድኑ ሰብሳቢ የሆኑት የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጎሳዬ ሽፈራው እንደገለፁት የኢንስፔክሽኑ ዋና አላማ እንደ ሀገር የሚገጥሙንን ፈተናዎች በድል ለመሻገር ጠንካራና መሰረት ያለው ተቋም ለመገንባት እንዲሁም የፓርቲ መደበኛ ስራዎችን በአደረጃጀትና በአሰራር መመሪያ መሰረት እየተሰሩ መሆኑን ለማረጋገጥ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዝግጅት ምዕራፍ ወቅት የተከናወኑ ተግባራትን በልዩ ወረዳና በተመረጡ ወረዳዎች በሰነድና በአካል እንደሚያረጋግጡ ተናግረዋል።