

፦የከተማ አስተዳደሩ የሱፐርቪዥን ኮሚቴ አባላት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ6 ወር የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን ሱፐርቪዥን ለማድረግ የተመደበው ኮሚቴ ከክፍለ ከተማ አስተባባሪና አጠቃላይ አመራር የጋራ በማድረግ በይፋ ስራ ጀምሯል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለተከታታይ 4ቀናት በክፍለ ከተማ 27 ሴክቶሮችና በክፍለ ከተማ ፓርቲ ተቋማት እንዲሁም በተመረጡ 3 ወረዳዎችና እስከ ብሎክ ድረስ ባሉ አደረጃጀቶች በተዘጋጀው ቸእሊስት መሰረት ተግባራትን የሚያረጋጌጥ ሲሆን በቀሪ 6ወራት ያልተሰሩ ዋና ዋና የህዝብንና የመንግስትን ትስስር የሚያጠናክሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱ ዘርፈ ብዙ የሆነ ጥቅም ያላቸውን ስራዎች ለመስራት ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
አስተዳደሩም በቅንጅት የተሰሩ እጅግ መልካም የሆኑ ተግባራቶችን ለማሳየትና የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቆይታው በአካልና በሰነድ እንዲያረጋግጣቸው ለማድረግ መዘጋጀቱን ለቲሙ አሳውቋል።