

በፌደራል ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመገኘት ስራውን ጀምሯል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው፣ሌሎች የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና የኮሚሽኑ አመራሮችና አማተሮች ለሱፐርቪዥን ቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ዋና አለማ ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን የስራ እንቅስቃሴና በ5 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ምልከታ በማድረግና ይበልጥ እንዲጠናከሩ አቅም ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በቆይታቸው በተመረጡ 2 ወረዳዎችንና ተቋማት ላይ ሱፐርቪዥን እንደሚያደረጉ ይጠበቃል።