Image placeholder
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ ቤት በ4 ዋና ዋና ነጦቦች ላይ በዙም ሚቲንግ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለወረዳና ለክፍለ ከተማ የፓርቲ ተቋማት አመራሮች ሰጥቷል።
By Belay | 2024-12-28

በግምገማው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦና ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደገለፁት ሳምንታዊ የፓርቲ የግንኙነት ጊዜን በዙም ቴክኖሎጂ በመገምገም የበለጠ ውጤታማነታችንን ማስቀጠልና ለላቀ ውጤት መነሳሳት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሃላፊው በግምገማቸው ወቅት ካነሱት ሀሳብ መካከል መደበኛ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች ላይ ያሉ አጠቃላይ ተግባራት የ2ቱ ሊጎችን የፋይናንስና የሚዲያን ጨምሮ፤ የአመራር ወቅታዊ ሁኔታ ፤ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሌብነት ትግልና የመልካም አስተዳደርና የህዝብ ጥያቄ የሚፈታበት አግባብ ፤ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ የንቅናቄ ተግባራት ፤አስተዳደሩ በ90 ቀን የሚፈፅማቸው የስራ ዕድል ፈጠራ፤የኑሮ ማረጋጋት፤የሌማት ቱርፋትና ሌሎች እቅዶች በስፋት የገመገሙ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ የወሰዱ ቸክሊስቶችና ቀሪ እቅዶችን በተደራጀ የአመራርና የአባል ስምሪት መፈፀም በሚያስችል ሁኔታ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

እንደ አቶ ይከበር ገለፃ ባሳለፍነው ግማሽ አመት በተረጋጋ የአመራር ስምሪት ውስጥ ሆነን የመጡ ለውጦቸን በማስቀጠል ለበለጠ ውጤት መነሳሳትና መትጋት ከብልፅግና አመራር የሚጠበቅ ነው ያሉ ሲሆን ሁሉንም ተግባር አቀናጅቶ በመምራት ሁለተናዊ ለውጥ እያመጣን የፓርቲን እግር እየተከልን መሄድ ያስፈልጋልም ብለዋል።

+9

የቅርብ ዜና


Loading...